[...]"እኔ አንድ ሀሳብ አለኝ።" ጓደኛዬ ኤፕሪል ምስጢር ለመናገር ስትፈልግ እንደምታደርገው ወደኔ ጠጋ አለ፤ምንም እንኳን እርሷ ጥሩ ምስጢር ባይኖራትም ወይም ምስጢሮቿ ከነጭራሹ ምስጢር የሚባሉ ባይሆኑም።"አንቺ ስለእኔ ለማንም ካልተናገርሽ፣ አይኖችሽን ላስተካክልልሽ እችላለሁ።"
"ከተማውን ለቀህ ውጣ!"
ዓይኖቹን ደጋግሞ አርገበገበ። "ለማድረግ እየሞከርኩ ያለውትም ይኽንኑ ነው።"
"ማለቴ አንተ ያንን ማድረግ አትችልም።"
"ለምንድን ነው የማልችለው?"
"እንግዲያውስ ከመነጽሮቼ በቀር ማንም ሰው ዓይኖቼን ለማስተካከል ስለማይችል።"
"እኔ የተወሰኑ ችሎታዎች አሉኝ።ያንን ደግሞ ታዪዋለሽ።ነገር ግን..."
"ስላንተ ለማንም አልናገርም ?"
"ዋናው ነጥብ ያ ነው።"
"ዓይኖቼን እንደማታጠፋብኝ በምን እርግጠኛ እሆናለሁ?ምናልባት ልክ እንደነዚያ የውሸት ቃል እንደሚገቡት ቴሌማርኬተሮች ልትሆን ትችላለህ።"
በድጋሜ ከወዲህ ወዲያ መንቀሳቀስ ጀመረ።"እኔ ምንም አይነት ጉዳት ያላደረሰብኝ ፍጥረት ላይ ያንን አላደርግም ።"
"እኔ ብጎዳህ ዓይኖቼ እንዲጠፋ ታደርጋህ ማለት ነው?"
"ያ አይነገርም፣ ምስጢር ነው።"
"እና አንተ አይኖቼን ከአስተካከልክልኝና እኔም ስላንተ ለማንም ካልተናገርኩኝ፣ማሳችንን ለቀህ ትወጣለህ?"
" እሱማ ዋናው ጉዳይ ነው።"